በሻሸመኔ ለ10 ቀናት በተደረገው ስብሰባ ህብረተሰቡ ከመጅሊሱ ጋር ስምምነት እንደደረሰ ተደርጎ መዘገቡ ስህተት መሆኑ ተገለፀ፡፡

· News Portal
Authors

አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 21/2004
ሻሸመኔ ከተማ መጅሊሱ ከመንግስት አካላት ጋር በመተባበር ህዝበ ሙስሊሙን ሰብስቦ ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና ከትላንት በስቲያ በመጠናቀቁን የሬዲዮ ቢላል ምንጮች አስታወቁ፡፡
በርካታ የሙስሙ ህብረተሰብ አካላት እንደተገኙበት በተገለጸው በዚሁ ስብሰባ ተሳታፊዎቹ ከተሰብሳቢዎቹ አካላት ጋር ሽብርተኝነትን በተመለከተ መንግስት አሸባሪዎ የሚላቸውን አካላት ሳያጣራ ስያሜ መስጠት እንደማይገባውም አሳስበዋል፡፡
ከስብሰባው መጠናቀቅ በኋላ ተሳታፊዎቹ ለጁምዐ ሰላት ለተሰበሰበው ህዝብ የስብሰባውን ፍሬ ሀሳብ መንገራቸው ተጠቁሟል፡፡
በዚህ ወቅት በመንግስት ሚዲያዎች ተሰብሳቢዎቹ ከሰበሰበው አካል ጋር ከስምምነት ደርሰዋል ተብሎ የተዘገበው ስህተት መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በተያያዘ ዜናም ሻሸመኔ አካባቢ በሚገኝ አንድ ትልቅ መስጂድ ውስጥ ጁምዐ የተሰበሰቡ ምዕመናን የመጅሊሱን አመራሮች እና የአህባሽን አስተምህሮ በመቃወም ተክቢራ ማሰማታቸውን ከምንጮቻችን ገላፃ ለመረዳት ተችሏል፡፡

Leave a comment