የአህባሽ እምነት አስተማሪዎች በጎንደር ታዋቂ ዳዒያንን ማክፈራቸው ህዝበ ሙስሊሙን አስቆጣ

· News Portal

አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 24/2004

ከሊባኖስ የመጡ ሁለት የአህባሽ እምነት አስተማሪዎች ሸህ ሱልጣን የተባሉ ኢትዮጵያዊ የእምነቱ አራማጅ ሰሞኑን በጎንደር ተገኝተው በሰጡት ገላጻ ወጣት ዳኢያንን ማክፈራቸው የከተማዋን ነዋሪዎች እንዳስቆጣ ተገለጸ፡፡

የአህባሽ አስተማሪዎች ባሳለፍነው ሳምንት በጎንደር ቀበሌ12 አካባቢ ከሚገኘው መስጂድ በርካታ የከተማዋ ሙስሊም ማህበረሰብ በተኙበት የእምነቱን አስተምህሮት ለመስበክ በተያዘላቸው ፕሮግራም ገለጻ አድርገው ነበር፡፡በዚሁ ገለጻቸው በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ዘንድ ሠፊ ተቀባይነት ያላቸውን ወጣት ዳዒያን ስም እየጠቀሱ በማክፈራቸው በወቅቱ የተሰበሰበውን ሙስሊም ማህበረሰብ ክፉኛ እንዳስቆጣ ነው በሥፍራው የሚገኙ የሬድዮ ቢላል ምንጮች የገለጹት፡፡

የእምነቱ አራማጆችና አስተማሪዎች ካሰፈሯቸው ዳዒያን መካከል ዳዒ ያሲን ኑሩ ዳዒ በድሩ ሁሴንና ዑስታዝ ሀሰን ታጁ ዋና ዋነዋናዎቹ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡እነዚህን ዳዒያን ባከፈሩበት ወቅት ሁከትና ግርግር ተከስቶ እንደነበረም ነው ምንጮቻችን ያስታወሱት፡፡በመጨረሻም በመስጅዱ ተሰባስበው የነበሩት ምዕመናን የከፈሩት ራሳቸው መሆናቸውን በመግለጽ ከመስጅዱ እንዳባረሯቸው ምንጮች ካደረሱን መረጃ ለመረዳት ተችሏል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በጎንደር ከተማ ቀኝ በር እየተባለ ከሚታወቀው መስጅድ ለበርካታ አመታት በኢማምነት ሲያገለግሉ የነበሩት ሸህ አሊ የአህባሽን አመለካከት በጽኑ በመቃወማቸው ከስራቸው እንዲባረሩ መደረጉን ምንጮቻችን አመልክተዋል፡፡  የአህባሽ መምህራንና ሰባኪያኑ ዳዒያንን በማክፈራቸው ብዙሀኑ የጎንደር ሙስሊም ማህበረሰብ በስልጠና መድረኮቻቸው ላይ አልተሳተፉም፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: