አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 24/2004
በኢትዮጲያ በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚማሩ ሙስሊም ተማሪዎች የዲን እንቅስቃሴአቸውን አበረታች እንደሆነ አስታወቁ፡፡ በሀገሪቷ የተለያዩ ዪኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ሙስሊም ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለሚመጡ ሙስሊም ተማሪዎች አቀባበል እንደሚያደርጉም ገልፀዋል፡፡
የተለያዩ ሙስሊም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በየካምፓሶቻቸው ኢስላማዊ እንቅስቃሴዎች የተሻለ አንደሆነ ይጠቁማሉ በተለያዩ ቋንቋዎች የዲን ትምህርቶች ሲሰጡ በአንድ የትምህርት ቦታ ላይ ብቻ ከ150-200 ተማሪዎች እንደሚማሩ አንድ የጅማ ዩኒቨርሲቲ አሚር እንዲህ ገልጾዋል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም የተማሪው ልዩነቶች እንደሚስተዋሉ አንድ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ጠቁማለች፡፡
በሙስሊሙ ማህበረሰብና በመጅሊስ በኩል በተፈጠረው ውዝግብ የዲን እንቅስቃሴው በአንዳንድ የዩኒቨርሲቲዎች ተቀዛቅዞ እንደነበረና በአሁኑ ወቅት ከሌላው ጊዜ በተሸለ መልኩ እየተሰራ እንደሆነ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተገኘነው መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡
Leave a Reply