አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 24/2004
በኢትዮጵያ የሙስሊምም ሆነ የክርስቲየን ተብለው የሚቋቋሙ ሀይማኖታዊ ባንኮች እንደማይኖሩ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አስታወቀ፡፡የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ባለፈው ሳምንት ዲያስፖራውን ባነጋገሩበት ወቅት የብሄራዊ ባንክ ገዢ ባቀረበላቸው ጥያቄ መልስ ሲሰጡ ነው ይህን ያስታወቁት፡፡
ከአንድ ዲያስፖራ የተጠየቀው ጥያቄ “እናንተ የተጠየቃችሁትን አትፈፅሙም አገር የጋራ ነው ሀይማኖት የግል ነው ትላላችሁ የዘምዘም ባንክ ምስረታ ለምን ተቋረጠ በገንዘብ በኩል የሙስሊም ሕዝብ ተሳትፎ እንዲጠናከር ለምን ጥረት አታደርጉም የሚል ነበር፡፡
ለጥያቄው መልስ የሰጡት የኢትዮጲያ ብሄራዊ ባንክ ገዢ አቶ ዩሃንስ አያሌው ኢትዮጲያ ውስጥ ኃይማኖት መሰረት አድርጎ የሚቋቋም ባንክ እንደማይኖር ገልፀዋል፡፡ ከወለድ ነፃ የሆነ ባንክ ለማቋቋም በምስረታ ላይ የነበረው የዘምዘም ባንክ አደራጆች በወቅቱ መምሪያ ባለመኖሩ ብሄራዊ ባንኩን ጠይቀው መመሪያ መውጣቱን አስታውቀዋል፡፡
ይህንኑ መመሪያ ተከትሎ ወደ አክሲዮን ሽያጭ በመግባት የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባሄ ማድረጉ ይታወቃል ፡፡በምስረታ ላይ የነበረው ዘምዘም ባንክ ጠቅላላ ጉባሄውን ቢያደርግም በብሄራዊ ባንክ ከወለድ ነፃ ባንክ መቋቋምን አስመልክቶ የወጣው የመጨረሻ መመሪያ በምስረታ ላይ የነበረው ባንክ ስራውን እንዳይቀጥል አድርጎታል ፡፡ በወቅቱ ብሄራዊ ባንክ ከወለድ ነፃ አገልግሎት የሚሰጥ ራሱን የቻለ ባንክ በኢትዮጲያ ማቋቋም እንደማይቻል ሁሉም ባንኮች ግን ከወለድ ነፃ አገልግሎት የሚሰጡበትን መስኮች እንደሚያደራጅ መዘገቡ አይዘነጋም፡፡
Leave a Reply