የኢትዮጲያ ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ለማስመለስ የሚደረገው ሠላማዊ ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ ፡፡

· News Portal
Authors

አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 22/2004

Dimtsachin Yisema ድምጻችን ይሰማ

Dimtsachin Yisema ድምጻችን ይሰማ

ኢትዮጲያውያን ሙስሊሞች ወቅታዊና ሕገመንግስታዊ የመብት ጥያቄዎች ለማስመለስ የተጀመረው ሰላማዊ ትግል ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባው የተለያዩ የአለማችን ሙስሊም ኮሚኒቲ አባላት ጠየቁ፡፡

በተለይ ለዘጠነኛጊዜ ቢላል ኮሚኒኬሽን ከመነ ተኩማ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ዘጠነኛው የድምፃችን ይሰማ አለም አቀፍ የውይይት መድረክ ተሳታፊዎች ናቸው ይህን የጠየቁት ፡፡   በአምስት መድረኮች ተከፋፍሎ ተከታታይአምስት ሰአታት በተካሄደውና በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ትዮጵያንና ተውልደ ኢትዮጲያውያን በተካፈሉበት በዚህ የውይይት መድረክ የተለያዩ የኮሚኒቲ አባላት የስራ ሪፖርታቸውን አቅርበዋል፡፡

ከነዚህም መካከል የሲውዘርላንድ፣ግብፅ፣አሜሪካና ሳዑድ አረቢያ የሚገኙ የኮሚኒቲ አባላት ይጠቀሳሉ፡፡   የኮሚኒቲ አባላቱ በሪፖርታቸው እንዳመለከቱት የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ሰላማዊ የትግል እንቅስቃሴ አቅጣጫ ለማስቀየር የሚደረገው ሙከራ መቆም አለበት፡፡    ሠላማዊ ትግሉ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና አቅጣጫውን ለማየት የሚደረጉ ሙከራዎች እንዲቆሙ የሚጠይቅ ሠላማዊ ሠልፍ በሰባት ታላላቅ የአለማችን ከተሞች እንዲካሄድም ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

በመጨረሻም በአርሲ ዞን አሳሳ ከተማ ሰሞኑን በተፈጠረው ሁከት ህይወታቸውን ላጡ ወንድሞች ጀነት ለቤተሰቦቻቸው ደግሞ መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡

የድምፃችን ይሰማ ዓለም አቀፍ የውይይት መድረክ በወቅታዊ የኢትዮጲያውያን ሙስሊሞች አጀንዳ ዙሪያ የሚያደርገው ውይይት ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የቢላል ኮሚኒኬሽን አስተዳደር ከደረሰን መረጃ ለመረዳት ተችሏል፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: