የምስራቅ ሀረርጌ 19 ወረዳ ነዋሪዎች የዑለማ ምክር ቤት አቋቋሙ በዲን ጉዳይ ፈትዋ የሚሰጡ አሊሞችንም ሠይመዋል፡፡

· News Portal
Authors

አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 22/2004

Harar የምስራቅ ሀረርጌ 19 ወረዳ ነዋሪዎች የዑለማ ምክር ቤት አቋቋሙ በዲን ጉዳይ ፈትዋ የሚሰጡ አሊሞችንም ሠይመዋል፡፡

በምስራቅ ሀረርጌ የ19 ወረዳ ነዋሪዎች የዑለማ ምክር ቤት ማቋቋማቸውና በዲን ጉዳይ ላይ ፈትዋ የሚሰጡ ዓሊሞችን መሰየማቸው ተገለፀ፡፡ ነዋሪዎች ትላንት በሐረር ከተማ ባካሄዱት ስብሰባ ሼህ አደም ቶላ ዋና ሙፍቲ አድርገው ሠይመዋል፡፡

ረዳት ሙፍቲ ደግሞ ሼህ ሙሳ ሳውላ  እንዲሆኑ ተመርጠዋል፡፡ በተጨማሪም በየወረዳው 15 አባላት የሏቸውን የዑለሞች ምክር ቤት ማደራጀታቸውን በስፍራው  የሚገኙ የሬዲዮ ቢላል ምንጮች ገልፀዋል፡፡

በወረዳቀው  ዑለሞቹ ምክር ቤት አባላት ፈትዋ የመስጠት ኃላፊነት ሲኖራቸው ሙፍቲዎቹ ደግሞ በዞን ደረጃ ፈትዋ እንደሚሰጡም ታውቋል፡፡ ሙፍቲህ መሰየማቸውና የዑለሞች ምክር ቤት መቋቋም ሕብረተሰቡ በአህባሽ አስተምህሮት የፈጠረበትን ብዥታ ለማጥራት እንደሚችልም ከምንጫችን ገለፃ ለመረዳት ተችሏል፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: