በአለም ገና የረያን መስጂድ የቁርአን ሂፍዝ ማዕከል መማሪያ ክፍሎች የቃጠሎ አደጋ ደረሰባቸው

· News Portal
Authors

አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 22/2004

በኦሮሚያ ልዩ ዞን ሰበታ ወረዳ አለም ገና ቀበሌ 02 ክልል ውስጥ የሚገኘው የረያን መስጂድ የቁርሃን ሂፍዝ ማዕከል አራት የመማሪያ ክፍሎቹ ከትላንት በስቲያ መሽት ቃጠሎ እንደደረሱባቸው ገለፁ ፡፡በአለም ገና ልዩ ስሙ ጅዳ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው የረያን መስጅድ አስተዳደር እንዳስታወቀው ከትላንት በስቲያ በኢሻ ሠላት ወቅት በደረሰው የቃጠሎ አደጋ ከ10ሺ ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት ወድሟል፡፡የረያን መስጂድ የተቋቋመው በአንድ ኢትዮጲያዊ አህለል ኽይር (በጎ አድራጊ)ግለሰብ ነው ፡፡ የዛሬ 5ዓመት ገደማ መስጂዱን ያቋቋሙት አቶ ሃይደር ሱልጣን እንዳሉት ከመስጂዱ አጠገብ የሚገኘው የመድረሳ   ትምህርት ቤት 40 ተማሪዎቸን በአዳሪነት ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡

የአካባቢው ማህበረሰብም ሆነ አስተዳደር አካላት እውቅና አግኝቶ በህጋዊ ካርታና ፕላን በይዞታው ባሰራቸው አራት የመማሪያ ክፍሎች ላይ ከትላንት በስቲያ ተማሪዎቹ በኢሻ ሰላት ላይ እያሉ ግን ድንገተኛ አደጋ ደረሰ፡፡ አደጋውን ያደረሱት ግለሰቦች ማንነት ለጊዜው በውል ባይታወቅም ስድስት ጭምብል ለባሽ ወጣቶች እንዳቃጠሉት በወቅቱ በአንደኛው ክፍል ውስጥ አሞት ተኝቶ የነበረው ተማሪ ከሰጠው እማኝነት ለመረዳት ችለናል ይላሉ፡፡ የተማሪውን አፍ በፕላስተር በማሸግና የማደንዘዣ መርፌ በመውጋት የመማሪያ ክፍሎቹን አቃጥለው መሮጣቸውንም ገልፀዋል፡፡

በወጣቶቹ አፈና የደረሰበት ተማሪ ድርጊቱን የፈፀሙት ወጣቶች ይህ የአልቃይዳና አሸባሪዎች መፈልፈያ ነው በማለት መናገራቸውን ገልፆዋል ብለዋል የመስጂዱና የመድረሳው መስራች አስተዳደር፡፡በማደሪያና መማሪያ ክፍሎች ላይ በደረሰው በዚሁ ቃጠሎ ግምታቸው ከ10 ሺ ብር በላይ የሆኑ አልባሳት ፍራሾች፣ቁርዓኖችና ኪታቦች መውደማቸውን ተናግረዋል፡፡ በአካባቢው ሕብረተሰብና የመስጂዱ ጀመዓ አባላት እሳቱን በውሃና በአፈር ለማጥፋት ባደረጉት ከአንድ ሰዓት በላይ የፈጀ ርብርብ ቃጠሎው ወደ መስጂዱ ሳይዛመት በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉንም ገልፀዋል፡፡

የመስጂዱ ጀመዓ አባላት እሳቱን ለማጥፋትና ርብርብ ላይ በመሆናቸው ድርጊቱን የፈፀሙት ግለሰቦች ተከታትሎ ለመያዝ ያደረጉት ሙከራ እንዳልተሳካላቸው ገልፀዋል፡፡ አደጋውን ያደረሱት ግለሰቦች ላይ ክትትል እንዲያደርግ ለአለም ገና ፖሊስ ጣቢያ አመልክተው ፖሊሶች ትላንት ጠዋት አካባቢውን ጎብኝተው መመለሳቸውን ጠቁመው መንግስት እንዲህ አይነት አፍራሽ ተልዕኮ ያላቸውን ግለሰቦች እንቆጣጠር ጠይቀዋል፡፡ በጉዳዩ የዓለም ገና ፖሊስ አባላት ምርመራ ላይ መሆናቸውን ከመግለፅ ውጪ ዝርዝር መግለጫ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: