በቄለም ወለጋ ዞን ከፍተኛ ወጪ ወጥቶበት ሊካሄድ የነበረው የዳዕዋ ፕሮግራም በመጅሊስ ትዕዛዝ ሳይካሄድ ቀረ

· News Portal
Authors

አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 22/2004

በቄለም ወለጋ ዞን ከ200ሺ ብር በላይ ወጪ ወጥቶበት ህብረተሰቡን ያስተምራል ተብሎ የተዘጋጀው የዳዕዋ ፕሮግራም መጅሊሱ ፍቃድ አልጠየቃችሁም በማለቱ ሳይካሄድ እንደቀረ በስፍራው የሚገኙ ምንጫችን ገለፀ፡፡ መጅሊሱ የዳዕዋ ፕሮግራሙን የከለከለው ለዞኑ አስተዳደር አካላት በፃፈው የእገዳ ደብዳቤ ነው፡፡

በርካታ ህዝበ ሙስሊም ይገኝበታል ተብሎ ይጠበቅ በነበረው በዚህ የዳዕዋ ፕሮግራም ላይ ከተለያዩ ወረዳዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ዓሊሞች ይሳተፉበት እንደነበር ነው የተገለጸው፡፡ ከፕሮግራሙ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ምሽት ላይ የመንግስት አካላት በስፍራው እንደተገኙ እና ድንኳኑ እንዲፈርስ ትዕዛዝ መስጠታቸው ተጠቁሟል፡፡

የአካባቢው ወጣቶች በመጅሊስ ድርጊት ተቆጥተው አላስፈላጊ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደነበርና በአካባቢው ሽማግሌዎች ምክርና ተግሳጽ ሁኔታው ሊረጋጋ እንደቻለም ምንጮች አመልክተዋል፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: