የሀገሪቱ ፖለቲካና የግዛት አንድነት ነክታችኋ ተብለው የተከሰሱ 3 ግለሰቦች የ19 ዓመት እስራት እንደተወሰነባቸው ተገለፀ፡፡

· News Portal
Authors

አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 20/2004
አልጋሚን አይዲለም ፣ሐሰን ዓሊ መሐመድና ዓብደል ቃድር መሐመድ የተባሉ ግለሰቦች ነው የሀገሪቱ ፖለቲካና የግዛት አንድነት በመንካት ወንጀል የፌደራሉ ዓቃቢ ህግ ክስ መስርቶባቸው የነበረው፡፡
ይህንኑ ተከትሎም ጥፋተኝነታቸው ተረጋግጧል በመባሉ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት እያንዳንዳቸው በ19 ዓመት ፅኑ እስራት እና ለአምስት ዓመት ከህዝባዊ መብቶቻቸው እንዲታገዱ ወስኗል ፡፡
የክስ መዝገቡ የሚመለከተው ደግሞ አንደኛ ተከሳሽ አልአሚን አይዲለም የአሸባሪ ቡድን አባል በመሆን ኤርትራ ከሚገኙ የአሸባሪ ቡድን ሃላፊዎች ጋር ግንኙነት ፈጥሯል የሚልና ሌሎች ማብራሪያዎችን የሚያትት ነው፡፡
ሁለትኛ ተከሳሽ ሐሰን ዓሊም በተመሳሳይ መልኩ ከ1999 ጀምሮ የአሸባሪ ቡድን አባል በመሆን ሲንቀሳቀስ እንደነበረና ሌሎች ጥፋቶች እንደተገኙበትም ጭምር ነው የተገለፀው፡፡
ሦስተኛው ተከሳሽም በተመሳሳይ መልኩ ሲንቀሳቀስ ነበር ነው የሚለው የክስ መዝገቡ፡፡
ሁሉም ተከሳሾች የወንጀል ድርጊቱን ዓላማ ውጤትና ፍሬ ሙሉ በሙሉ በመቀበል ሲሳተፉ ነበር የሚል ክስ ቀርቦባቸው ነው ጥፋተኛ ናችሁ ተብው የ19 ዓመት ፅኑ እስራት እና  ለ5 ዓመት ከህዝባዊ መብቶቻቸው እንዲታገዱ የተደረገው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: