በአሳሳ ትልቁ መስጂድ አካባቢ በተፈጠረው ግርግር የሟቾችና ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር በውል አለመታወቁ ተነገረ፡፡

· News Portal
Authors

አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 20/2004
ዛሬ በከተማዋ አንፃራዊ ሠላምና መረጋጋት መኖሩንም ተጠቁሟል፡፡
በአርሲ ዞን አሰሳ ከተማ ትላንት ከጁም ሰላት በኋላ የሟቾች እና  ጉዳት የደረሰባቸው  ሰዎች ቁጥር በትክክል አለመታወቁን ለአካባቢው ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለፁ፡፡
በአሰሳ  ከተማ ትልቁ መስጂድ አካባቢ ሠላት እንደተጠናቀቀ በፀጥታ ኃይሎች ይፈለግ የነበረን አንድ የዳዕዋ ሰው ለመያዝ ፖሊሶች ባደረጉት ጥረት በህብረተሰቡ የገጠመውን ተቃውሞ ተከትሎ ሦስት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን መሰገባችን ይታወሳል ፡፡ይሁንና የሟቾቹ ቁጥር ከዚህ ሊበልጥ እንደሚችል ለአሰሳ ከተማ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልፀዋል፡፡
የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉንና አስክሬናቸው ወደ አዲስ አበባ እንደተላከ እየገለፁ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የሟቾች ቁጥር ሰባት መድረሱንና የአራት ሰዎ አስክሬን ወደ አዲስ አበባ መላኩን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
ከአሰሳ ትልቁ መስጂድ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑትን ሸህ አቡበከር በተደጋጋሚ በስልክ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም  ፡፡
የአሰሳ ከተማ አስተዳደርና የፀጥታ ኃይሎችን ለማግኘት ያደረግነውም ጥረት እንደዚሁ፡፡
በአካባቢው ያሉ ምንጮች እንደገለፁልን የተፈጠረውን ግርግር ተከትሎ የሟቾቸች ከባድና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ቁጥር አስከአሁን በትክክል ለማወቅ እንዳልተቻለ ነው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የከተማው ነዋሪ የሆነ አንድ ወጣት በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ እንደሌለው ገልጾ በከተማዋ ግን አንፃራዊ ሠላምና መረጋጋት መኖሩን ገልጾዋል፡፡
የፀጥታ ኃይሎች የሚወስዱት እርምጃ ህግና ስርዓትን የተከተለ ሊሆን እንደሚገባ እንድ የሕግ ምሁር ገለፁ
አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 20/2004
የፀጥታ ኃይሎች የህብረተሰቡን ሠላምና መረጋጋት ለማስጠበቅ በተጣለባቸው ኃላፊነት የሚወስዱት እርምጃ ሕግና ስርዓት የተከተለ ሊሆን እንደሚገባው አንድ የሕግ ምሁር ገለፁ፡፡
ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የህግ ምሁር በሠጡት አስተያየት ለምንና እንዴት እንደተፈለጉ በተረጋጋ መልኩ የማስረዳት ኃላፊነት አለባቸው፡፡
ከዚህ ውጪ በስሜትና በኃይል ተጠርጣሪዎችን ለማቅረብ የሚደረጉት እንቅስቃሴዎች ሕጋዊ አካሄድ ያለመሆኑን ነው የህግ ምሁሩ የገለፁት፡፡
ማህበረሰቡም ሆነ ተጠርጣሪው ግለሰብ ለፀጥታ ኃይሎች ሕጋዊና ስርዓት ላለው ጥያቄ ያለመታዘዝ ብሎም የኃይል አፀፋ ለመመለስ በሌለበት ሁኔታ የፀጥታ ኃይሎች መሳሪያ መተኮስ እንደማይችሉም አስረድተዋል፡፡
ከዚህ መሰረታዊ መርህ በመነሳት ትላንት በአሰሳ ከተማ የተፈጠረው ችግር ተገቢው ማጣራት ሊደረግበት እንደሚገባ ነው የህግ ምሁሩ ያብራሩት
-በመሆኑም ከሶስቱ የፀጥታ ኃይሉን የተኩስ እርምጃ እስከ ማስወሰድ የሚያሰወስን መሆን ያለመሆኑ በሕግ አግባብ መጣራት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: