የመፍትሄ አፈለላጊ ኮሚቴው ለመንግስት ከፍተኛ አመራር አካላት የኢትዮጲያውያን ሙስሊሞች የመብት ጥያቄን እንዲመልሱ ጥያቄውን አቀረበ

· News Portal
Authors

አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 19/2004

        በህዝብ የተወከለውና 17 አባላት ያሉት የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው መንግስት ለኢትዮጲያ ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ተገቢው ምልሽ እንዲሰጥ በደብዳቤ በድጋሚ መጠየቁ ተገለፀ፡፡

ኮሚቴው ሁለት ገፅ ደብዳቤ በመንግስት በኩል እየተንፀባረቀ ያለው የተዛባ አመለከካከት እንዲስተካከል ይረዳሉ ያላቸውን ማብራሪያዎች አካቷል፡፡ ደብዳቤውን ለ10 የመንግስት አስፈፃሚ አካላት ማስገባቱም ይታወቃል፡፡

የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴው በደብዳቤው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ መደጋገም የእምነት መብት ጥያቄን ሕገወጥ አያደርገውም ብሏል፡፡ ኢትዮጲያውያን ሙስሊሞች በኢትዮጲያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መሪነት የተፈፀመው የእምነት ነፃነት ጥሰት በይፋ ሲቃወሙ አራት ወራት ሆኗቸዋል ሲልም አስታውሷል፡፡

ይሁንና በእነዚህ ወራት ማስመዝገብ የተቻለው ያማረ አካሄድን እንጂ ያማረ ውጤትን አለመሆኑን ጠቅሷል፡፡

የህዝቡ ጥያቄም ሆነ አቀራረቦች ምንም ዓይነት የይዘት ለውጥ ሳይኖራቸው አንዳንድ የመንግስት ባለስልጣናት የማዋከብና የማሸማቀቅ አመለካከቶች ከየት ሊመነጩ እንደሚችሉም ጠይቋል፡፡

እነዚህ አመለካከቶች የመነጩት ከመንግስት ነው ወይስ መስመራቸውን ከለዩ ባለስልጣናት በሚል አቅጣጫው ባለየለት መንታ መንገድ ላይ እንደሚገኝም ገልፀዋል፡፡

በመሆኑም እነዚህንና ሌሎች መሰረታዊ ነጥቦች ላይ ያሉትን ተጨባጭ ሁኔታዎች የሚዳስስ 22 ገጽ የግንዛቤ ማስጨበጫና የዳግም ጥያቄአችን መልስ ያግኝ አቤቱታ ያካተተውን ይህን ደብዳቤ ማዘጋጀት ማስፈለጉን ነው ኮሚቴው የገለፀው፡፡

ይህን ደብዳቤ በአጠቃላይ ለመላው የሀገሪቱ ዜጎች በተለይም ደግሞ ለኢትዮጲያውያን ሙስሊሞች ለማዳረስ በሚየስችሉ አማራጮች ሁሉ እንደሚበትንና እንደሚያስተላልፍ አስታውቋ፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: