በታላቁ አንዋር መስጂድ በዛሬው ጁምዓ ምዕመናን ተቃውሟቸውን አሰሙ

· News Portal
Authors

አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 19/2004

        በዛሬው የጁምዓ ሰላት በአንዋር መስጂድ ከ30 ሺ በላይ የሚጠጉ ምዕመናን በመጅሊስ አመራሮች ላይ የተቃውሞ ድምፃቸውን አሰምተዋል፡፡

በአንዋር መስጂድና በአካባቢው ለጁምዓ ሰላት የተሰበሰበው ሙስሊም ህብረተሰብ ከጁምዓ ሰላት በኋላ ለ30 ደቂቃዎች ያህል በተክቢራ የተቃውሞ ድምፃቸውን ሲያስተጋቡ ታይቷል፡፡

በመስጂዱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ካሰሟቸው መፈክሮች መካከል ድምፃችን ይሰማ፣መጂሊስ ይውረድ፣መብታችን ይከበር የሚሉት ይጠቀሳሉ፡፡ ከአንዳንድ ሰጋጆች ለመረዳት እንደተቻለውም ብዛት ያለው ሙስሊም ህብረተሰብ ከተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ድምፁን ለማሰማት በታላቁ አንዋር መስጂድ ተገኝቶ ነበር፡፡

አንድ አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው በየተቃውሞው ተክቢራ ምን እየተደረገ እንዳልገባቸውና በመስጂድ ውስጥ እንደዚህ ዓይነት ተቃውሞ መደረጉን እንዳልወደዱት ጠቁመዋል፡፡

በዚሁ ታላቁ አንዋር መስጂድ የተቃውሞ  ድምፃቸውን ሲያሰሙ ከነበሩት መካከል ወረቀት በትናችኋል፣የተቃውሞ ቀስቃሽ ናችሁ በሚል በየጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች መታሰራቸውን የአካባቢው ታማኝ ምንጮች ለማወቅ ተችሏል፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: