በድሬደዋ አቅራቢያ በምትገኘው መልካጀብዱ ከተማ መጅሊስ ከመንግስት አካላት ጋር በመተባበር ሊያካሂድ ያሰበው ስልጠና እንዳልተሳካለት ተነገረ

· News Portal
Authors

አዲስ አበባ ሬዲዮ ቢላል ሚያዚያ 17/2004
ዛሬ ጠዋት መጅሊስ ከመንግስት ጋር በመተባበር በመልካ ጀብዱ ከተማ አክራሪነትና “ፅንፈኝነት” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ በተሰጠ ስልጠና ህዝቡ ከመጅሊስና ከመንግስት አካላት ጋር ሳይስማማ መበተኑን ከስፍራው የሚገኙ ምንጮች ገለፁ፡፡
በስልጠናው መግቢያ ላይ ከመድኩ ህገ መንግስቱን ያማከለ ስልጠና እንደተሰጠ ህዝቡ የመጂሊሱን አመራሮች እና የመንግስትን ጣልቃ ገብነት በመቃወም አስተያየቱን እንደሰጠ ነው የተገለፀው፡፡
ስልጠናው ላይ የተሳተፉ በአካባቢው እውቅና ያላቸው አንድ አዛውንትን መንግስት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ምላሽ የሰጠበት አግባብ እንዳልነበረና የመጅሊሱን ምርጫ ህዝቡ እንዲያካሂድ አለመመቻቸቱ አግባብ እንዳልሆነ መግለፃቸውም ተጠቁሟል፡፡
በስብሰባው የተሳተፈው ከ500 በላይ የሚሆን ህዝበ ሙስሊምም አስተያየት የሚሰጡ ሰዎችን ሀሳብ በተክቢራ ሲደግፍ እንደነበረም ተገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም የመጅሊስ እና የመንግስት አካላት የስልጠናውን አቅጣጫ ለመቀየር ሲሞክሩ የተሰበሰበው ህዝብ ተክቢራ እያሰማ አዳራሹን ጥሎ መውጣቱን በስፍራው የተገኙ ምንጮቻችን አብራርተዋል፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: